ኢትዮጲያዊ

የደብረዘይት ልጆች አንዴት ናችሁ፡፡ እኔ ሰላም ነኝ፡፡ ከደብረዘይት ናፍቆት እና ሃሳብ በስተቀር ይመስገነው፡፡ የደብረዘይት ናፍቆት እንዴት አደረብህ ብትሉኝ ወደ ኃላ 4ት አመት ከምናምን ወራት ትመልሱኛላችሁ፡፡ ወደ ግንቦት 10፣2000 ዓ.ም፡፡ የሰርጌ እለት፡፡ ሰርጌ አዲስ አበባ ሆኖ አዳሬ ደብረዘይት ወደሆነበት እለት፡፡ ይቅርታ አዳሬ ከምል አዳራችን ማለት አለብኝ፡፡ አዳራችን የእኔና የሙሽሪት፡፡ የአሁን የልጄ እናት የወ/ሮ ሰላማዊት በቀለ፡፡ ለ 10 ቀናት በሸፈነው የጫጉላ ሽርሽራችን ወቅት ከተጠቀምንባቸው ቦታዎች መካከል የደብረዘይቱ የመኮንኖች ክበብ አንዱ ነበር፡፡ በድጋሜ ወደ ክበቡ የገባሁት ታህሳስ 14፣2005 ዓ.ም ነበር – ለስብሰባ፡፡ ከስብሰባው ሰዓት በፊት ለምሳ እዚያው መከንኖች ክበብ ታደምን፡፡ ምሳ በልተን እስክንወጣ የታዘብነው አንድ ነገር – የአስተናጋጆች ቅልጥፍናን ነበር፡፡ እጅግ ቀልጣፎች የሚመስሉ ነገርግን በተቃራኒው የሆኑ አስተናጋጆች፡፡ በአጭር ቃል የአስተናጋጁች ውብ የደንብ ልብስ እና ደምግባት ያላቸው መሆናቸው ለመስተንግዶው ደምግባትነት አልተመነዘርም፡፡ እዚህ አዲስ አበባ የሚገጥመኝ ተመሳሳይ ነገር ያስታወሰኝ መስተንግዶ፡፡ በውበታቸው የተመሰገኑ ወይንም አዲስ በሚል ስም እየተጠሩ ዘመነኞች የሚገበያዩባቸው የአዲስ አበባ ህንጻዎች አንድ የሚጎድላቸው ነገር አለ፡፡ እርሱም የህንጻው ውበት እና በህንጻው ውስጥ በተለያየ ሁኔታ የሚሰሩ ውብ ሰራተኞች በተለይም ውብ ሴቶች የአግልግሎት አሰጣጣቸው ውበተ-ቢስ መሆናቸው ነው፡፡ እንዴት ይደብራል መሰላችሁ!ምኑ? ውብ ህንጻውስጥ፣ ውብ ሰራተኞችን ቀጥሮ ግን ውብ አገልግሎቶችን መስጠት አለመቻል! መኮንኖች ቁጥር 1 በብዙ ትዝታ ውስጥ ሆኜ ገባሁ፡፡ ግን ተበሳጭቼ ወጣሁ፡፡ በተንቀራፈፈው መስተንግዶ፡፡ ምግብ አዘን እስኪመጣ የወሰደው ጊዜ፣ ገንዘብ ለመክፈል ጠይቀን ሂሳብ እስኪመጣ ድረስ ከገጠመን ጊዜ ጋር አንድ መሆኑ ነው፡፡ አንድ ነገር አዛችሁ እስኪመጣ የሚወስድባችሁ ጊዜ አንድ መጽሄት ማንበብ ከጀመራችሁ እንድታገባድዱ ሊያደርጋችሁ ይችላል፡፡ ምሳው አለቀእና ወደተከፈለበት የመሰብሰቢያ አዳራሽ አመራን፡፡ ሌላው የክበቡ መስተካከል ያለበት ገጽታ ገጠመን፡፡ የተከፈለበት አዳራሽ አልተስተካከለም፡፡ እንደተዝረከረከ ነው፡፡ ሌላ ክፍል ተቀየረ፣ በተጨማሪ ክፍያ፡፡ እኛው ቤቱን አስተካከልን፣ ወንበሩን ደርድረን፡፡ ለተለዋጩ ክፍል ተጨማሪ 200 ብር ከፍለን ወጣን፡፡ ከደብረዘይቱ መኮንኖች ቁጥር 1፡፡ የደብረዘይት ልጆች እንዴት ናችሁ፡፡ እኔ ሰላም አይደለሁም፡፡ ከደብረዘይት መልካም መስተንግዶ እጦት በስተቀር ይመስገነው፡፡ ደብረዘይትን – ደብረትጉሃን ያድርግልን፡፡ አሜን፡፡

Advertisements

ዘለቀ ደገለ፣ ወዳጄ! ጋብቻውን ፈጸም፡፡ በእለቱ በማስተባበር ሞከርኩ፡፡ ብዙ ከባድ ነገሮች በእለቱ ገጥሞኝ ነበር፡፡ ከባድ ነገሮቹ መካከል ለሰርጉ ብዬ የገዛሁት እና ከእዚህ በፊት ያላደረኩት ጫማ የፈጠረብኝ የህመም ስቃይ አንዱ ነው፡፡ ፕሮግራሙን በሰዓት ለመምራት ያለመቻል ችግር ሌላው ነው፡፡ የሰዓቱ ጉዳይ የሚጀምረው እኔ ዘግይቼ ሙሽራው ቤት ከደረስኩበት ነው፡፡ መሪ የሌለው አይን የለውም እንደምለው፡፡ የአስተባባሪው በሰዓት በሚገባው ቦታ አለመድረሱ የሰዓት ክፍተቶቹ መነሻ ነበር፡፡ ከእዚህ በመቀጠል የካሜራ ባለሙያዎች ትእዛዝ ለመቀበል አለመፍቅድ ሌላው ችግር ነው፡፡ በተለይም ሙሽሪት ቤት እና ግዮን ውስጥ ከካሜራ ባለሙያዎች ጋር የፈጠርኩት አታካሮ ከባዱ ጊዜ ነበር፡፡ ከግዮን ወጥተን ወደ ጉዲና ቱምሳ አመራን፡፡ የቃልኪዳን ስነስርኣቱ ላይ ጸሎትን፣ ዝማሬን እና የቃል አቅርቦትን ያቀረቡት አገልጋዮች በሰዓት በመጠቀም አሪፍ ነበሩ፡፡ ሙሸሪት/ተስፋ ጽዮን/ ያሳደገቻቸው ልጆች የዘመሩት መዝሙር እጅግ ውብ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ የለስላሳ እና የኬክ አቅርቦት መዘግየት ተጨማሪ ሃሳብ ሆኖብኝ ነበር፡፡ በስተመጨረሻ ዘሌ እና ተስፉ ተጋቡ፡፡ እግዚአብሔር ጋብቻቹሁን ይባርክ፡፡ የሰርጉ እለት ምሽት በተደረገው የዳቦ ስም ለማውጣት በተደረገው ስርዓት ከቀረቡት ስሞች መካከል “በለስ” የሚለው ስም የሙሽሪት የዳቦ ስም ሆኖ ተመረጠ፡፡ ዘሌ እና በለስ መልካም ዘመን ይሁንላቸው ዘንድ ተመኘሁ፡፡ በዛሬው የመልስ ስነስርዓት ላይ ስለመገኘቴ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ያልተጋባችሁ ተጋቡ፣ ግራ የተጋባችሁ ኑ! እንወያይ፣ ግራ የምታጋቡ እራሳችሁን ፈለጉ ተመለሱም፣…የተጫጫችሁ ውሳኔን አሳልፉ … ብዙ ተባዙም …!!!

ትላንት ዲሴምበር 19፣2012 እለተ ማክሰኞ ከስራ መልስ በቀጥታ ያመራነው ወደ ቦሌ ሸዋ ዳቦ አከባቢ ወደሚገኘው ቤተዛታ ሆስፒታል ነው፡፡ እኔ ልታከም፣ የስራ ባልደረባዬ ጌትነት አለበል ሊያሳክመኝ፡፡ ታከምኩ፣ ዶ/ሩ ምግብ መመገብ እንዳለብኝ መከረኝ፡፡ እኔም ምክሩን ተግባራዊ ለማድረግ አሰብኩ፡፡ ከቤተ ዛታ የተቀበልኩት ደረሰኝ “Please Come Again”/”እባክዎ ተመልስው ይምጡ” የሚል መልእክት ይነበብበታል፡፡ ፈገግ አልኩ፡፡ መቼም ዶ/ሮቹ በሽተኛ እንዲበዛ የሚሰሩ አይመስለኝም፡፡ እንደ ምግብ ቤት ተመልሳችሁ ጎብኙን ብለው እንደማይጠብቁም አስባለሁ፡፡ ከጌትነት እና ከሌሎች የሆስፒታሉ ሰራተኞች ጋር በጽሁፉ ላይ ተሳሳቅንበት፡፡ ቤተ ዛታ ተመልሶ መሄድ ችግር የለበትም ግን ታሞ መሄድ አልፈልግም፡፡ ተሸሎኝ ግን ጠቅላላ ጤንነቴ ምን እንደሆነ በየጊዜው ለመከታተል ብሄድ እመርጣለሁ፡፡ በጤና ጊዜ ወደ ሆስፒታል የመሄድ ባህል ለሌለው እኔ እንዳለሁበት አይነት ማህበረሰብ እርሱም የማይታሰብ ይመስላል፡፡ ዛሬ የሄድኩት በስራ ባልደረባዬ ወዳጄ ጌትነት እና ሌሎች የቢሮ ባልደረቦቼ ግፊት ነው፡፡ ለማንኛውም ወደ ቤተዛታ ስለመመለሴ እርግጠኛ ባልሆንም፣ የቦሌ መንገድ ጉዳይ ግን ሌላው ያለመመለሴ ምክንያት ነው፡፡ መንገዱ ፈርሶል ሳይሆን ፈራርሶል ማለት ይቀላል፡፡ ያ ቀውጤው የደምበል ሰፈር፣ ዛሬ በዝምታ ተውጦል፡፡ አቤት ይሄ መንገድ ባለቀጊዜ ምን እንደሚፈጠር፣ ለማየት ያብቃን….ያኔ እመለስ ይሆናል፡፡ ባማረ መንገድ፣ በጤናማነት ስሜት፣ በሚስቴ እና በልጄ ታጅቤ የቤተሰቤን ጤንነት ለመከታተል ወደ ቤተ-ዛታ እመለስ ይሆናል፡፡ ምንም እንኳን “Please Come Again”/”እባክዎ ተመልስው ይምጡ” የሚለው ጽሁፍ በህክምና ተቋማት ደረሰኝ ላይ መገኘት እንዳለበት ባላምንበትም፡፡

በቅድሚያ እንኳን የጀመራችሁትን ለመጨረስ ቻላችሁ እያልኩ ሦስት ነጥቦችን ከእዚህ በታች በምክር መልክ ለማስቀመጥ እወዳለሁ፣

1.    ስራ መፈለግ እራሱን የቻለ ስራ መሆኑን እናስተውል!

ተመረቅን ማለት ስራ አገኘን ወይም ስራ ጀምርን ማለት አይደለም፡፡ ይህ ማለት ካልሆነ አሁንም የቤተሰቦቻችን ድጋፍ፣ አሁንም በሌሎች እገዛ እራስን ለመቻል የሚደረገው ጥረት ይቀጥላል ማለት ነው፡፡

ምናልባት በትምህርት ቤት ቆይታችን ጠንክረን በመስራት ወይም ለማለፊያ የሚሆን ውጤት ለማግኘት ብቻ በመስራት፣ ብዙም ተግቶ ባለማጥናት ቆይተን ይሆናል፡፡ አሁን ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ ከባድ ስራ ከፊታችን አለ፡፡ እርሱም ስራ መፈለግ ነው፡፡ ስራ መፈለግ እራሱን የቻለ ስራ መሆኑን ልንረዳ ይገባናል፡፡ ለምን ስራ መፈለግ እራሱን የቻለ ስራ ነው ተባለ?

  1. ስራ ለማግኘት ማልደን ወጥተን የስራ ማስታወቂያ የሚወጣባቸውን መንገዶች መጎብኘት ስለሚኖርብን፣
  2. ለስራ ለማመልከት ማመልከቻ ማዘጋጀት፣ የመረጃችንን ምጥን (Curriculum Vitae) ማዘጋጀት ስለሚኖርብን፣
  3. ለመወዳደር ፈተና መቀመጥ፣ ስራ ጥያቆ/Interviewee) ማድረግ ስለሚኖርብን፣
  4. ስራ ባይገኝስ የሚለውን የስነ-ልቦና ውጥረት በአግባቡ መቆጣጠር ስለሚኖርብን፣

ስለዚህ ስራ መፈለግ እራሱን የቻለ ስራ መሆኑን ተገንዝበን ወገባችንን ታጥቀን መሰማራት ይኖርብናል፡፡

2.   ስራ ስንፈልግ ስልታዊ መሆን እንደሚኖርብን እናስተውል!

ስራ የቤታችንን በር አንኳኩቶ የመምጣት እድሉ እጅግ አናሳ ነው፡፡ ኸረ እንደውም የማይታሰብ ነው፡፡ ስለዚህ ስራ በመፈለግ ሂደት ስልታዊ መሆን ይኖርብናል፡፡

ስራ የሚለጠፍባቸው ቦታዎችን፣ የስራ ማስታወቂያ የሚያወጣባቸውን የህትመት ውጤቶችን እና  ድህረ-ገጾችን በአግባቡ መከታተል አንዱ የስልታዊነት መገለጫ ነው፡፡

ስለዚህ በመጀመሪያ ስራ የሚወጣባቸውን ቦታዎችን፣ የህትመት ውጤቶችን እና ድህረ-ገጾችን ለማወቅ በመሞከር ዝርዝራቸውን በማስታወሻ ላይ በመጻፍ ልንይዝ ይገባል፡፡

የእኔን ጥቆማ ከእዚህ በታች ለመነሻ ያህል ላስቀምጥ፣

ቦታዎችለምሳሌ፡ አዲስ አበባ ውስጥ ለምትፈልጉ 4ት ኪሎ ፓስታ ቤት አከባቢ (ከ4ት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ዝቅ ብሎ)፣ ሜክሲኮ ፓስታ ቤት አከባቢ (ከሸበሌ ጋርደን ጥቂት ዝቅ ብሎ)፣

የሕትመት ውጤቶች፡- ጋዜጦች፡ 1. ሪፓርተር የእሁድ እትም፣ …

ድህረ ገጾች፡

www.ethiojobs.net,

www.ethioworks.com

www.ezega.com/Jobs

www.employethiopia.com

www.thereporterjobs.com

ከእዚህ በላይ በተጠቀሱት ድረ-ገጾች ላይ መረጃችንን ለመጫን (Upload) ለማድረግ ኢ-ሜል ስለሚያስፈልገን በቅድሚያ ኢ-ሜል ከሌለን ኢ-ሜል መክፈት ይኖርብናል፡፡ የኢ-ሜል አገልግሎት ከሚሰጡት ድርጅቶች መካከል yahoo እና google የነጻ አገልግሎት ከሚሰጡት መካከል ቀዳሚዎች ናቸው፡

3.   ቀጣሪ ባይገኝስ ብለን እናስተውል!

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አስቸጋሪ እየሆነ ከመጣው የአለም አቀፍ ኢኮኖሚ ውድቀት ብዙ ድርጅቶች የሰዎችን ቁጥር በመቀነስ አገልግሎት መስጠት፣ ምርት ማቅረብ የሚቻልባቸውን መንገዶች እየነደፉ እና እየተገበሩ ይገኛሉ፡፡ የቴክኖሎጂው እድገትም የሰውሃይልን በማሽን በመተካት እየተገለጠ ይገኛል፡፡

ሪፓርተር ጋዜጣ ጁላይ 4፣2012/ሰኔ 27፣2004 ዓ.ም ባወጣው ዜና “ዲግሩ ያላቸው ዜጎች የጎዳና ተዳዳሪዎች ሆነዋል” ሲል ዘግቦል፡፡

ስለሆነም ቀጣሪዎች ላይገኙ እንደሚችሉ ማሰብ የግድ ይላል፡፡ቀጣሪ የለም ማለት ግን ሥራ የለም ማለት አይደለም፡፡ዓለማችን ሥራ የማይኖርባት አለም የምትሆንበት ጊዜ ይመጣል የሚል እምነትም የለም፡፡

መሰራት ሲኖርባቸው ግን ሳይሰሩ የሚቀሩ የቤተሰብ ጉዳዮች፣ የማህበረሰቡ ጉዳዮች፣ የሃገር ጉዳዮች ወዘተ ብዙ ስራዎች ሰሪዎችን እየጠበቁ መሆናቸውን ያስረዳል፡፡ ጥያቄው የሚሰራውን ስራ ለመጀመር እራስን ስለሚሰራው ስራ በእውቀት ማስታጠቅ፣ ካለን የትምህርት እውቀት ጋር ማዛመድ እና ስራው በመሰራቱ የስራው ተጠቃሚዎች ሊከፍሉበት እንዲችሉ ማሳመን ነው፡፡ የስራው ተጠቃሚዎች የቤተሰብ አባሎቻችን፣ የማህበረሰቡ ሰዎች፣ የከተማው ነዎሪዎች፣ የአገሪቱ ዜጎች፣ የድርጅት ሰራተኞች ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ስለዚህ ቀጣሪ ባይገኝስ በሚል ከወዲሁ በራሳችን ወይንም ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን መስራት የምንችላቸውን ስራዎች ማሰብ፣ ለተግባራዊነቱ እንቅስቃሴን ማድረግ፣ ስራውን በህጋዊነት ከመስራት አንጻር የሚያስፈለጉ የሃገሪቱን ደንቦች፣ መመሪያዎች ወይም ህጎች ለማወቅ መሞከር ያስፈልጋል፡፡

ማጠቃለያ

በድጋሚ እንኳን ለምረቃ አበቃችሁ እያልኩ ስራ በመፈለግ ሂደት ውስጥ ስራ መፈለግ እራሱን የቻለ ስራ መሆኑን መረዳት፣ ስራ ስንፈልግ ስልታዊ መሆን እንደሚሆንብን መረዳት እና ቀጣሪ ባይገኝስ ብሎ በማሰብ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ከእዚህ በላይ ተመልክተናል፡፡

ቀጣሪ እስኪገኝ ወይንም የራስ ስራ እስኪጀምር ድረስ የነጻ አገልግሎት በመስጠት ልምድ ለማግኘት መሞክር በዚህ ወቅት መደረግ ከሚገባቸው ነገሮች መካከል አንዱ ነው፡፡

በስተመጨረሻ፣ ኢ-ሜል ለመከፈት እና የስራ ማስታወቂያ የሚወጣባቸውን ድረ-ገጾች ለማግኘት ከእዚህ በታች የተዘረዘሩትን ድረ ገጦች ጽሁፎቹ ላይ በመጫን ድረ-ገጾቹን ማግኘት እንችላለን፡፡

  1. gmail ለመክፈት
  2. yahoomail ለመክፈት
  3. የስራ ማስታወቂያ ለማንበብ

ethiojobs    ethioworks    ezega     employethiopia    thereporterjobs

  1. የኢትዮጲያ ገቢዎች ጉምሩክና ባለስልጣን ስራዎችን ለማግኘት

መልካም የሥራ ፍለጋ ወይም የሥራ ፈጠራ ጊዜ ይሁንልን!

ሐብታሙ ኪታባ/0911-913311/

ትላንት፣ ዛሬ እና ነገ ጤናማ ሲሆኑ ህይወት በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ በሰላም የተሞላ ይሆናል፡፡ ትላንት በትዝታ የተሞላ ነውና ትላንትን ስታሰብ ጤንነት እንዲሰማህ ትላንትህን አሳክም፡፡ ትላንትን የሚያክም አንድ አለ እርሱም…፡፡ ዛሬን ስትኖር በደስታ ለመሆን የምትደግፍበት ያስፈልግሃል፡፡ የምትቆምበት መቆሚያ ያሻሃል፡፡ መደገፊያ እና መቆሚያ ያለው እንዴት ፍርሃት ያገኘዋል፡፡ እንዴት ደስታውስ ይናጋል፡፡ ስለዚህ በዛሬ ጠዋት፣ በዛሬ ቀትር፣ በዛሬ ምሽት ልትደገፍበት የምትችል አንድ አለ እርሱም…፡፡ ነገ የተስፋ መገለጫ ነው፡፡ በነገ ላይ ያለህ ተስፋ የዛሬህን ደሰታ ይወስነዋል፡፡ ነገ ተስፋ የምታደርገው፣ በእርግጥም የምታምነው ተስፋ አለህ? ካለህ መልካም ነው፡፡ ብዙ አይነት ነገ አለ፡፡ ከዛሬ ቀጥሎ ያለው ቀጣዩ ቀን ነገ፡፡ ከእዚህ ሳምንት ቀጥሎ የሚመጣው ሳምንት ነገ፡፡ ከእዚህ ወር ቀጥሎ ያለው ወር ቀጥሎ ያለው ወር ነገ፡፡ ከእዚህ አመት ቀጥሎ የሚመጠው አመት ያለው አመት ቀጥሎ ያለው አመት ነገ፡፡ ከእዚህ ህይወት ቀጥሎ ያለው ሕይወት ቀጥሎ የሚመጣው ከሞት ባሻገር ያለው የዘላለም ነገ፡፡ ከነገው ነገ እስከ ዘላለሙ ነገ ድረስ ልታምነው የምትችለው ተስፋ በእርገጥ አለህ? ካለህ ዛሬን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ማለትም በማግኘት በማጣት፣ በ…በ፣ በ…በ፣ በደስታ እና በተረጋጋ ህይወት ውስጥ እንዳትኖር የሚከለክልህ አይኖርም፡፡ ከነገው ነገ ጀምሮ እስከ ዘላለሙ ነገ ድረስ ልትደገፍበት የምትችል፣ ሙሉ ደስታህ ሊሆን የሚችል፣ ከሁኔታ ባሻገር መኖር እንድትችል የሚያደርግ አንድ አለ እርሱም…፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የነገህን ሃጢአት በደሙ ማንጻት የሚችል፣ ለዛሬ ህይወትህ መደገፊያ መሆን የሚችል፣ ስለ ዘላለሙ ነገህ መተማመኛ መሆን የሚችል በዘማናት መካከል ትውልድን ያነጋገር የመፍትሄዎች ሁሉ ፍጹሙ መፍትሄ የትላንት፣ የዛሬ እና የነገ ሃኪም፡፡ እርሱ ታወቀው ይሆናል – በአእምሮህ፡፡ በአእምሮህ ያወከው ሁሉ፣ በልብህ ያለነው ማለት አይደለምና ወደ ልብህ አውረደህ ጎደኛ አድረገህ ያዘው፡፡ ለበለጠ መረጃ ከተከታዮቹ መካከል አንዱ የነበረው ተከታዩ ዩሐንስ የከተበውን እዚህ ላይ በመጫን እንድታነብ እጋብዝሃለሁ፡፡ ይህን ጽሁፍ ስለምወድህ ጻፍኩልህ፡፡ የምስራች ብዬዋለሁ፡፡ Cheers!

የቢሮ ባልደረባዬ መሰረት አበበ ከወንድሞ ጋር በስልክ እያወራች ነው፡፡ እርሱ ለስራ ጉዳይ ወደ ከፍለሃገር ሄዶል፡፡ እርሶ ስራውን ከጀመረ በኃላ እንደሚፈልገው አላገኘውም መሰል ማዘን ጀምሯል፡፡ መሰረተ ደጋግማ አትቸኩል እያለችው ነው፡፡ ዛሬ ግን አንድ የገረመኝን ንግግር ነገረቸው፡፡ ለውጥ የሚጀምረው ከአእምሮ ነውና፣ እራስህን በቅድሚያ አሳምን አለችው፡፡ እርግጥ ነው ለውጥ የአስተሳሰብ ውጤት ነው፡፡

አለማችንን የቀየሩ ታላላቅ ሰዎች መነሻቸው ማሰባቸው ነው፡፡ ማሰብ፣ መፍትሄን መፈለግ፡፡ ማሰብ፣ ለችግር ፍቺውን መፈለግ፡፡ ማሰብ…

ለውጥ የሚጀመርው ከማሰብ ነው!

ለውጥ…!

Thinking Like a Leader

Don’t copy the behavior and customs of this world, but let God transform you into a new person by changing the way you think.

Romans 12:2

Some years ago a magazine pictured a man staring out of a window; the caption read: “Why does this company pay this man $100,000 to look out a window?” The answer: Because the lifeblood of any organization lies in ideas and creative thinking. Thinking is powerful. Flying a plane, air conditioning, cell phones, vaccines, the World Wide Web–without thinking, these would have been impossible. Everything begins with a simple thought.

Ideas are a great moving force of history. We are never free to do what we cannot conceive. Having a godly mind enlarges our thinking capacity. A leader’s thinking must be shaped by the following:

Vision: What is our dream? Carl Sandburg was right: “Nothing happens unless it is first a dream.” Vision is a process of the mind–it’s mental, not visual. Vision is seeing what everybody has seen but thinking what nobody has thought. What is needed to build a pyramid? One person who can think and ten thousand people who can grunt.

Values: What is important? Values have to do with how we treat people, how we do our work, what is vital to us. Values are the standards, the principles, and the code of conduct that characterize the organization. Values aren’t dreamt; they already exist. Leaders shape and form the organization’s values. Some universities decide to pour sidewalks after students have first worn a path. Where are the well-worn paths–the actions, the beliefs, the attitudes–that matter most to you? Those are your values.

Venture: What are we willing to risk? Organizations that make a difference are willing to think outside the box. For example, a company that was in the well-digging business began to think in terms of efficient and effective means of making holes, and they soon discovered that lasers dug holes better than augers. They achieved the same goal but accomplished it more efficiently.

Vehicle: What will get us there? How can we accomplish our desired outcome? A dream without a strategy is merely wishful thinking, but with a strategy it becomes powerful thinking.

Victory: What will the celebration be like? A leader thinks like a champion. The end result is to move forward, to accomplish goals, to be God’s faithful servant, to celebrate being a part of God’s kingdom.

Wake up and start thinking. Take off your nightcap and put on your thinking cap. Ask God to continually renew your mind.

Forwarded by: Habtamu Kitaba

Prepared by: Tyndale House Publishers © 2011 351 Executive Drive, Carol Stream Illinois 60188

Tag Cloud