ኢትዮጲያዊ

መደመር መቀነስ፣ ማባዛት ማካፈል

ደውል ተደወለ፣ ሰልፍም ተካሄደ

መዝሙር ተዘመረ፣ባንዲራም ከፍ አለ

ተማሪው ገባና፣መምህሩ ደረሰ

***    ***   ***   ****

ትምህርት ተጀመረ፣ እውቀት ተላለፈ

መደመር መቀነስ፣ ከሁሉ ሰረጸ

ሲደመር ሲቀነስ፣ ሲቀነስ ሲደመር ጊዜው ነጎደ…ጊዜው አለቀ

***    ***   ***   ****

መምህሩ ፈገገ፣ ደግሞም እዝን አለ

ማባዛት፣ ማካፈል ሳያስተምር ቀረ…ጊዜያው አለቀ

የዋሁ ተማሪ በደስታ ጨፈረ፣ በደሰታ ሰከረ

ለምን ከተባለ

በቃ…ተመረቀ

በቃ…ሱፍ ለበሰ

በቃ…ተመረጠ

በህዝብ ጉዳይ ላይ መናገር ጀመረ

***    ***   ***   ****

ማለዳ ሰመነው፣ ቀትርም አየነው፣ ምሽት አነበብነው

የስሌቱን ውጤት ሚዲያ ዳሰሰው

ሚዲያ ደመረው፣ ሚዲያም ቀነሰው

ዳግም እንዲደምር፣ ዳግም እንዲቀንስ በደንብ አስተማረው

ማባዛት ማካፈል ለምን ሊበጀህ፣ ለምንህ ሊሆንህ ብሎም አሳመነው፡፡

***    ***   ***   ****

ቋንቋን አደባልቆ፣በድብልቅ ቃላት በጽልመት ተናግሮ

ከአሁኑ ተጣልቶ፣ በአሁኑ ተመስጦ

ሲደምር ሲቀንስ ዘመኑን የፈጀ

ብዜት ማካፈልን በእርግጥ ያላወቀ

በርከት ያለትውልድ መንገድ ላይ ቀረ፡፡

ሐብታሙ ኪታባ

ጁን 21፣ 2011/ሰኔ 14፣2003 ዓ.ም

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

Tag Cloud

%d bloggers like this: