ኢትዮጲያዊ

Archive for the ‘ልዩ ልዩ’ Category

መኮንኖች ቁጥር 1፣ ደብረዘይት

የደብረዘይት ልጆች አንዴት ናችሁ፡፡ እኔ ሰላም ነኝ፡፡ ከደብረዘይት ናፍቆት እና ሃሳብ በስተቀር ይመስገነው፡፡ የደብረዘይት ናፍቆት እንዴት አደረብህ ብትሉኝ ወደ ኃላ 4ት አመት ከምናምን ወራት ትመልሱኛላችሁ፡፡ ወደ ግንቦት 10፣2000 ዓ.ም፡፡ የሰርጌ እለት፡፡ ሰርጌ አዲስ አበባ ሆኖ አዳሬ ደብረዘይት ወደሆነበት እለት፡፡ ይቅርታ አዳሬ ከምል አዳራችን ማለት አለብኝ፡፡ አዳራችን የእኔና የሙሽሪት፡፡ የአሁን የልጄ እናት የወ/ሮ ሰላማዊት በቀለ፡፡ ለ 10 ቀናት በሸፈነው የጫጉላ ሽርሽራችን ወቅት ከተጠቀምንባቸው ቦታዎች መካከል የደብረዘይቱ የመኮንኖች ክበብ አንዱ ነበር፡፡ በድጋሜ ወደ ክበቡ የገባሁት ታህሳስ 14፣2005 ዓ.ም ነበር – ለስብሰባ፡፡ ከስብሰባው ሰዓት በፊት ለምሳ እዚያው መከንኖች ክበብ ታደምን፡፡ ምሳ በልተን እስክንወጣ የታዘብነው አንድ ነገር – የአስተናጋጆች ቅልጥፍናን ነበር፡፡ እጅግ ቀልጣፎች የሚመስሉ ነገርግን በተቃራኒው የሆኑ አስተናጋጆች፡፡ በአጭር ቃል የአስተናጋጁች ውብ የደንብ ልብስ እና ደምግባት ያላቸው መሆናቸው ለመስተንግዶው ደምግባትነት አልተመነዘርም፡፡ እዚህ አዲስ አበባ የሚገጥመኝ ተመሳሳይ ነገር ያስታወሰኝ መስተንግዶ፡፡ በውበታቸው የተመሰገኑ ወይንም አዲስ በሚል ስም እየተጠሩ ዘመነኞች የሚገበያዩባቸው የአዲስ አበባ ህንጻዎች አንድ የሚጎድላቸው ነገር አለ፡፡ እርሱም የህንጻው ውበት እና በህንጻው ውስጥ በተለያየ ሁኔታ የሚሰሩ ውብ ሰራተኞች በተለይም ውብ ሴቶች የአግልግሎት አሰጣጣቸው ውበተ-ቢስ መሆናቸው ነው፡፡ እንዴት ይደብራል መሰላችሁ!ምኑ? ውብ ህንጻውስጥ፣ ውብ ሰራተኞችን ቀጥሮ ግን ውብ አገልግሎቶችን መስጠት አለመቻል! መኮንኖች ቁጥር 1 በብዙ ትዝታ ውስጥ ሆኜ ገባሁ፡፡ ግን ተበሳጭቼ ወጣሁ፡፡ በተንቀራፈፈው መስተንግዶ፡፡ ምግብ አዘን እስኪመጣ የወሰደው ጊዜ፣ ገንዘብ ለመክፈል ጠይቀን ሂሳብ እስኪመጣ ድረስ ከገጠመን ጊዜ ጋር አንድ መሆኑ ነው፡፡ አንድ ነገር አዛችሁ እስኪመጣ የሚወስድባችሁ ጊዜ አንድ መጽሄት ማንበብ ከጀመራችሁ እንድታገባድዱ ሊያደርጋችሁ ይችላል፡፡ ምሳው አለቀእና ወደተከፈለበት የመሰብሰቢያ አዳራሽ አመራን፡፡ ሌላው የክበቡ መስተካከል ያለበት ገጽታ ገጠመን፡፡ የተከፈለበት አዳራሽ አልተስተካከለም፡፡ እንደተዝረከረከ ነው፡፡ ሌላ ክፍል ተቀየረ፣ በተጨማሪ ክፍያ፡፡ እኛው ቤቱን አስተካከልን፣ ወንበሩን ደርድረን፡፡ ለተለዋጩ ክፍል ተጨማሪ 200 ብር ከፍለን ወጣን፡፡ ከደብረዘይቱ መኮንኖች ቁጥር 1፡፡ የደብረዘይት ልጆች እንዴት ናችሁ፡፡ እኔ ሰላም አይደለሁም፡፡ ከደብረዘይት መልካም መስተንግዶ እጦት በስተቀር ይመስገነው፡፡ ደብረዘይትን – ደብረትጉሃን ያድርግልን፡፡ አሜን፡፡

Advertisements

ለውጥ የሚጀምረው፣…

የቢሮ ባልደረባዬ መሰረት አበበ ከወንድሞ ጋር በስልክ እያወራች ነው፡፡ እርሱ ለስራ ጉዳይ ወደ ከፍለሃገር ሄዶል፡፡ እርሶ ስራውን ከጀመረ በኃላ እንደሚፈልገው አላገኘውም መሰል ማዘን ጀምሯል፡፡ መሰረተ ደጋግማ አትቸኩል እያለችው ነው፡፡ ዛሬ ግን አንድ የገረመኝን ንግግር ነገረቸው፡፡ ለውጥ የሚጀምረው ከአእምሮ ነውና፣ እራስህን በቅድሚያ አሳምን አለችው፡፡ እርግጥ ነው ለውጥ የአስተሳሰብ ውጤት ነው፡፡

አለማችንን የቀየሩ ታላላቅ ሰዎች መነሻቸው ማሰባቸው ነው፡፡ ማሰብ፣ መፍትሄን መፈለግ፡፡ ማሰብ፣ ለችግር ፍቺውን መፈለግ፡፡ ማሰብ…

ለውጥ የሚጀመርው ከማሰብ ነው!

ለውጥ…!

Tag Cloud