ኢትዮጲያዊ

Posts tagged ‘gaming’

ለ አዲስ ተመራቂዎች፣

በቅድሚያ እንኳን የጀመራችሁትን ለመጨረስ ቻላችሁ እያልኩ ሦስት ነጥቦችን ከእዚህ በታች በምክር መልክ ለማስቀመጥ እወዳለሁ፣

1.    ስራ መፈለግ እራሱን የቻለ ስራ መሆኑን እናስተውል!

ተመረቅን ማለት ስራ አገኘን ወይም ስራ ጀምርን ማለት አይደለም፡፡ ይህ ማለት ካልሆነ አሁንም የቤተሰቦቻችን ድጋፍ፣ አሁንም በሌሎች እገዛ እራስን ለመቻል የሚደረገው ጥረት ይቀጥላል ማለት ነው፡፡

ምናልባት በትምህርት ቤት ቆይታችን ጠንክረን በመስራት ወይም ለማለፊያ የሚሆን ውጤት ለማግኘት ብቻ በመስራት፣ ብዙም ተግቶ ባለማጥናት ቆይተን ይሆናል፡፡ አሁን ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ ከባድ ስራ ከፊታችን አለ፡፡ እርሱም ስራ መፈለግ ነው፡፡ ስራ መፈለግ እራሱን የቻለ ስራ መሆኑን ልንረዳ ይገባናል፡፡ ለምን ስራ መፈለግ እራሱን የቻለ ስራ ነው ተባለ?

  1. ስራ ለማግኘት ማልደን ወጥተን የስራ ማስታወቂያ የሚወጣባቸውን መንገዶች መጎብኘት ስለሚኖርብን፣
  2. ለስራ ለማመልከት ማመልከቻ ማዘጋጀት፣ የመረጃችንን ምጥን (Curriculum Vitae) ማዘጋጀት ስለሚኖርብን፣
  3. ለመወዳደር ፈተና መቀመጥ፣ ስራ ጥያቆ/Interviewee) ማድረግ ስለሚኖርብን፣
  4. ስራ ባይገኝስ የሚለውን የስነ-ልቦና ውጥረት በአግባቡ መቆጣጠር ስለሚኖርብን፣

ስለዚህ ስራ መፈለግ እራሱን የቻለ ስራ መሆኑን ተገንዝበን ወገባችንን ታጥቀን መሰማራት ይኖርብናል፡፡

2.   ስራ ስንፈልግ ስልታዊ መሆን እንደሚኖርብን እናስተውል!

ስራ የቤታችንን በር አንኳኩቶ የመምጣት እድሉ እጅግ አናሳ ነው፡፡ ኸረ እንደውም የማይታሰብ ነው፡፡ ስለዚህ ስራ በመፈለግ ሂደት ስልታዊ መሆን ይኖርብናል፡፡

ስራ የሚለጠፍባቸው ቦታዎችን፣ የስራ ማስታወቂያ የሚያወጣባቸውን የህትመት ውጤቶችን እና  ድህረ-ገጾችን በአግባቡ መከታተል አንዱ የስልታዊነት መገለጫ ነው፡፡

ስለዚህ በመጀመሪያ ስራ የሚወጣባቸውን ቦታዎችን፣ የህትመት ውጤቶችን እና ድህረ-ገጾችን ለማወቅ በመሞከር ዝርዝራቸውን በማስታወሻ ላይ በመጻፍ ልንይዝ ይገባል፡፡

የእኔን ጥቆማ ከእዚህ በታች ለመነሻ ያህል ላስቀምጥ፣

ቦታዎችለምሳሌ፡ አዲስ አበባ ውስጥ ለምትፈልጉ 4ት ኪሎ ፓስታ ቤት አከባቢ (ከ4ት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ዝቅ ብሎ)፣ ሜክሲኮ ፓስታ ቤት አከባቢ (ከሸበሌ ጋርደን ጥቂት ዝቅ ብሎ)፣

የሕትመት ውጤቶች፡- ጋዜጦች፡ 1. ሪፓርተር የእሁድ እትም፣ …

ድህረ ገጾች፡

www.ethiojobs.net,

www.ethioworks.com

www.ezega.com/Jobs

www.employethiopia.com

www.thereporterjobs.com

ከእዚህ በላይ በተጠቀሱት ድረ-ገጾች ላይ መረጃችንን ለመጫን (Upload) ለማድረግ ኢ-ሜል ስለሚያስፈልገን በቅድሚያ ኢ-ሜል ከሌለን ኢ-ሜል መክፈት ይኖርብናል፡፡ የኢ-ሜል አገልግሎት ከሚሰጡት ድርጅቶች መካከል yahoo እና google የነጻ አገልግሎት ከሚሰጡት መካከል ቀዳሚዎች ናቸው፡

3.   ቀጣሪ ባይገኝስ ብለን እናስተውል!

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አስቸጋሪ እየሆነ ከመጣው የአለም አቀፍ ኢኮኖሚ ውድቀት ብዙ ድርጅቶች የሰዎችን ቁጥር በመቀነስ አገልግሎት መስጠት፣ ምርት ማቅረብ የሚቻልባቸውን መንገዶች እየነደፉ እና እየተገበሩ ይገኛሉ፡፡ የቴክኖሎጂው እድገትም የሰውሃይልን በማሽን በመተካት እየተገለጠ ይገኛል፡፡

ሪፓርተር ጋዜጣ ጁላይ 4፣2012/ሰኔ 27፣2004 ዓ.ም ባወጣው ዜና “ዲግሩ ያላቸው ዜጎች የጎዳና ተዳዳሪዎች ሆነዋል” ሲል ዘግቦል፡፡

ስለሆነም ቀጣሪዎች ላይገኙ እንደሚችሉ ማሰብ የግድ ይላል፡፡ቀጣሪ የለም ማለት ግን ሥራ የለም ማለት አይደለም፡፡ዓለማችን ሥራ የማይኖርባት አለም የምትሆንበት ጊዜ ይመጣል የሚል እምነትም የለም፡፡

መሰራት ሲኖርባቸው ግን ሳይሰሩ የሚቀሩ የቤተሰብ ጉዳዮች፣ የማህበረሰቡ ጉዳዮች፣ የሃገር ጉዳዮች ወዘተ ብዙ ስራዎች ሰሪዎችን እየጠበቁ መሆናቸውን ያስረዳል፡፡ ጥያቄው የሚሰራውን ስራ ለመጀመር እራስን ስለሚሰራው ስራ በእውቀት ማስታጠቅ፣ ካለን የትምህርት እውቀት ጋር ማዛመድ እና ስራው በመሰራቱ የስራው ተጠቃሚዎች ሊከፍሉበት እንዲችሉ ማሳመን ነው፡፡ የስራው ተጠቃሚዎች የቤተሰብ አባሎቻችን፣ የማህበረሰቡ ሰዎች፣ የከተማው ነዎሪዎች፣ የአገሪቱ ዜጎች፣ የድርጅት ሰራተኞች ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ስለዚህ ቀጣሪ ባይገኝስ በሚል ከወዲሁ በራሳችን ወይንም ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን መስራት የምንችላቸውን ስራዎች ማሰብ፣ ለተግባራዊነቱ እንቅስቃሴን ማድረግ፣ ስራውን በህጋዊነት ከመስራት አንጻር የሚያስፈለጉ የሃገሪቱን ደንቦች፣ መመሪያዎች ወይም ህጎች ለማወቅ መሞከር ያስፈልጋል፡፡

ማጠቃለያ

በድጋሚ እንኳን ለምረቃ አበቃችሁ እያልኩ ስራ በመፈለግ ሂደት ውስጥ ስራ መፈለግ እራሱን የቻለ ስራ መሆኑን መረዳት፣ ስራ ስንፈልግ ስልታዊ መሆን እንደሚሆንብን መረዳት እና ቀጣሪ ባይገኝስ ብሎ በማሰብ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ከእዚህ በላይ ተመልክተናል፡፡

ቀጣሪ እስኪገኝ ወይንም የራስ ስራ እስኪጀምር ድረስ የነጻ አገልግሎት በመስጠት ልምድ ለማግኘት መሞክር በዚህ ወቅት መደረግ ከሚገባቸው ነገሮች መካከል አንዱ ነው፡፡

በስተመጨረሻ፣ ኢ-ሜል ለመከፈት እና የስራ ማስታወቂያ የሚወጣባቸውን ድረ-ገጾች ለማግኘት ከእዚህ በታች የተዘረዘሩትን ድረ ገጦች ጽሁፎቹ ላይ በመጫን ድረ-ገጾቹን ማግኘት እንችላለን፡፡

  1. gmail ለመክፈት
  2. yahoomail ለመክፈት
  3. የስራ ማስታወቂያ ለማንበብ

ethiojobs    ethioworks    ezega     employethiopia    thereporterjobs

  1. የኢትዮጲያ ገቢዎች ጉምሩክና ባለስልጣን ስራዎችን ለማግኘት

መልካም የሥራ ፍለጋ ወይም የሥራ ፈጠራ ጊዜ ይሁንልን!

ሐብታሙ ኪታባ/0911-913311/

Advertisements

Tag Cloud